የአገልግሎታችን ትኩረት

• የመንግስቱን ወንጌል በሬዲዮን፣ በኢንተርኔት፣ በግልና በጽሑፍ ማሰራጨት።
• በጸጋው ወንጌል ላይ የተመሠረተ አገልግሎት መስጠት።
• ጌታን ሊከተሉ የወሰኑትን በጸጋው ቃል ማሳደግ።
• መንፈሳዊ የሆነውን የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ሕብረት መጠበቅ።
• በምልጃና በልመና ጸሎት ስለ ሐገራችን፣ ስለ ሕዝባችንና ስለ ሰዎች ልጆች ሁሉ በመማለድ ማገልገል።
• ድሖችንና ችግረኞችን በረድኤት አገልግሎት ማገዝ።
• ለምንኖርበት ሐገር እንግዳ በመሆን የሚቸገሩትን በምክርና በሚያስፈልጋቸው ሁሉ መርዳት።
• ያልተበረዘና ያልተከለሰውን የኢየሱስን ወንጌል ከሚያገለግሉ ጋር በወንጌል ሥራ መተባበር።

ማዕከላዊ እሴቶቻችን

• ልጁን በመስጠት ፍቅሩን ለገለጠልን አባት፣ በቀራንዮ መስቀል ሞቶ በመነሳት ላዳነን ለናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የርስታችን መያዣ ሆኖ በልጅነት መንፈስ ለሚያኖረን መንፈስ ቅዱስ፥ አንድም ሶስትም ለሆነው ስሉስ ቅዱስ ለሆነው አንድ አምላክ በፍቅር፣ በእምነትና በተስፋ እየተገዛን እናመልከዋለን።
• ጌታችን ሁሉን አዲስ ለማድረግ አሮጌውን ያሳለፈበትን የመስቀሉን ሥራ ባማከለ አገልግሎት ማገልገል።
• አማኞች ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን እንዲሆኑ የሚፈለገውን የጌታን ሃሳብ የጠበቀ መንፈሳዊ እድገት እንዲኖራቸው ቤተ ክርስቲያን የተማከለችበትን ሕይወትና አገልግሎት እንዲያስተውሉ ማስተማርና መምራት።
• “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደባችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ” በሚለው የጌታ ቃል ላይ ተመስርተን በኃጢያት፣ በልማድና በተለያየ ነገር መንፈሳዊ ሕይወታቸው የተጎሳቆለባቸውንና የዛለ ሕይወት ያላቸውን በጌታ ፍቅር እየተቀበልን ጌታን አምነው እንዲድኑ፣ በጸጋው ሐይል እንዲታደሱና እንዲታደሱ ማገልገል።
• ለወንጌል እንቅፋት ከሆነ ሕይወት፣ አሰራርና አገልግሎት ራሳችንንና ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ እናገለግላለን።
• በመልካም ወሬና በክፉ ወሬ ሳንበገር በሰይጣንም ውጊያ ሳንረበሽ ሁሉን ለበጎ የሚያደርግልንን ጌታችንን ታምነን በእምነትና በምሥጋና ሕይወት የሚደግፈንን ጌታን በመታመን እናገለግላለን።